TEMSALET m jun, 2015 | Page 4
ይህ አምድ በቀዳሚነት የሚዘክረው በስራቸው
ስኬታማነት በዓለማችን ላይ በጎ ተጽእኖን ማሳደር
የቻሉ ግለሰቦችን እንዲሁም ተቋማትን ይሆናል
አክራሞት
“ከኢትዮጵያ ስወጣ
እድሜ እቀንሳለሁ”
መምህርነት
የተከበረ
ሙያ ነው!
በዝግጅት ክፍሉ
ለ
በዝግጅት ክፍሉ
ዛ
ሬ የሰሞኑ ዓብይ ርዕስ አድርገን
የምናነሳው ጉዳይ “ክብርና
ምስጋና ለመምህራን“ በሚል
መርህ በመዲናችን በሚገኘው
አፍሪቃ ሕብረት አዳራሽ ለአዲስ አበባ
የመንግስት ት/ቤቶች መምህራን የተሰጠውን
የክብር እና የምስጋና ሽልማት ነው፡፡
ሽልማቱ “Invest on teachers, Invest
on future” በሚል መሪ ቃል በዓለም ዓቀፍ
ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ የተከበረውን የመምህራን
ቀን ተከትሎ የተከናወነ መሆኑ ይታወሳል ፡፡
በአዲስ አበባ ለሚገኙ የመንግስት ት/ቤቶች
መምህራን ለሁለተኛ ጊዜ የተሰጠው ይህ
ሽልማት ዓላማ ያደረገው በጥቅሉ በትምህርት
ስራ የተሰማሩ መምህራንን ውለታ ለመዘከር
እና ታታሪ የሆኑትን የበለጠ ለማበረታታት
ታስቦ እንደሆነ በመርሃ ግብሩ ተጠቅሷል ፡፡
ሽልማቱ የመምህራንን ተነሳሽነት ለመፍጠር&
በማሕበረሰቡ ዘንድ ለመምህራን ያለውን
ክብር የበለጠ ለማጎልበት & ለሙያው
ፍቅር ለመስጠት& ቅብብሎሹን ለትውልዱ
ለማሸጋገር እንዲሁም የትምህርት ጥራትን
በማስጠበቅ ስራ ፈጠራና ተወዳዳሪ ዜጎች
ለማፍራት ነው ፡፡
በወቅቱም በሙያው ላይ የሚገኙና
3
በአፈጻጸማቸው ተመዝነው ውጤታማ ለሆኑ
120 መምህራን እና የአገልግሎት ዘመናቸው
35 ዓመታት እና ከ700 የሚበልጡ
መምህራን የሜዳሊያና የምስክር ወረቀት
እንዲሁም ልዩ ልዩ የማበረታቻ ሽልማቶችን
ሰጥቷል ፡፡
በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ የሚገኙ
መምህራን በሚያበረክቱት አስተዋጽዎ
ለአንድ አገር ህልውና መሰረት የሚሆን
ትውልድ በማፍራት እና በመቅረጽ ረገድ
የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ ፡፡ መምህራን
ለተማሪዎቹ የሚሰጠት ትምህርት ስኬታማነት
አንጻራዊ በሆነ መልኩ የሚወሰነው
በትምህርት ዝግጅታቸው በማስተማር
ለሙያው ባላቸው ፍቅር መሆኑ የማይካድ
ነው፡፡
በቀድሞ ዘመን ስለሙያው ክብር እንዲ ሲባል
መዜሙ የሚዘነጋ አይደለም፡፡
“የኛ ሙሽራ ኩሪ ኩሪ አገባች አስተማሪ
የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው በእንግሊዝ አፍ
አናግሪያቸው”
ይህ ጣዕመ ዜማ በመምህራን ጆሮ በኩራት
ከተደመጠ በትንሹ አራት አስርታትን
አስቆጥሯል ፡፡ተንደርድሮ ወንበር ላይ ቁብ
ያለውን ድርግ በትቢያ የጣለውን መምህርነት
የኛ ተምሳሌት
ሙያ ሞልቶለት ከውድቀት የሚታደገው
ከቶም አልተገኘም፡፡
አሁን “መምህራኖቻችንን እናክበር” መባሉ
ከሰሞንኛ ግርግር እንዲያም ሲል ለወቅታዊ
ድል ግብዓትነት ከመዋል አልፎ በእርግጥ
ታስቦበት ከሆነ ሃሳቡ ራሱ ክብር የሚገባው
ነውና መጨረሻውን ያሳምረው እንላለን ፡
፡ ሽልማቱን አስመልክቶ ያሉትን ጠቂት
ክፍተቶች ጠቃቅሰን ሃሳባችን እንቋጫለን፡፡
የክብና የምስጋና ሽልማቱ ጅማሬ
የመበረታታቱን እና የመመሰገኑን ያህል
እንከኖቹም የዚያኑ ያህል ለትችት
አጋልጠውታል ፡፡ የመጀመሪያው አገር አቀፍ
ተደራሽ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን የግል ት/
ቤቶች መምህራንን አለማካተቱ በአሉታዊነት
የሚጠቀስ ነው፡፡ ከዚያም ባለፈ ለብዙ
ዓመታት ብስቁልና በሚበዛበት በዚህ ሙያ
ውስጥ ቆይተው በጡረታ የተገለሉ አንቱ
የተባሉ አንጋፋ መምህራን አለማሳተፉ
አግባብነት ያለው አይመስለንም፡፡ በመሆኑም
እንዲህ አይነቱ ምስጋናና ሽልማት እጅግ የበዛ
ጥንቃቄ ካልታከለበት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ
የሚያመዝን እንደሆነ በእጅጉ ሊታሰብበት
ይገባል እንላለን ፡፡
እናትነት ወግ ያልበቃች እናት የጎስቋላዊቱን
ምድር ጨልማ ለብሳ ትቃትታለች፡፡ ገና ዘመነ
ቡረቃዋን ሳትጨርስ በሰቅጣጭ አካላዊ ህመምና
በማህበራዊ ሴፍ መሰየፍን በመሳሰሉ ሁለትዮሽ
ስቃዮች በመፈተን ላይ ያለች ቀንበጥ ያለማቋረጥ እሪታዋን
ብታቀልጠው አይፈረድባትም፡፡ ለምን ቢባል በጨቅላይቱ
የጨቅላ እናት ላይ የዘመተው ደዌ ፌስቱላ ነዋና ኡኡታን
ያለማሰለስ ኡኡ ቢያስብል የተገባ ነው፡፡ ዳሩ የዘመናት የፍዳ
ምች ሁለመናዋን እያማታት ያለው አዛውንቷ ኢትዮጵያ
የእንቦቀቅላይቱን እዬዬ መስማት የሚቻላት አይነት
አልነበረችም፡፡ እናም በፌስቱላ እስር የታሰረች ይህቺ አሳዛኝ
እናት ባንድ ፊት ህመሟን በተስፋ ቢስነት እያስታመመች
በሌላ ወገን ማህበራዊ ጥቂታን ከአቅሟ በላይ እያስተናገደች
ባለችባት አገሯ ሰማይ ላይ “ካትሪን” የተባለች ጸሀይ
ሳትታ b,8biH8bixbaH8b