TEMSALET m jun, 2015 | Page 2

በውስጥ የተምሳሌት አቋም በሀገራችን የዘመናዊ ትምህርት ከተጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡ ፡ ይሁንና በየዘመናቱ በተግባር ላይ የዋሉት የትምህርት ስርአቶች ተገቢውን የባህሪ ለውጥ በማምጣት እረገድ ፍሬያማ ነበሩ ለማለት በእጅጉ ይቸግራል፡፡ በእርግጥ የትምህርት ስርአቶቻችን ውጤታማ ሆነው ቢሆን ኖሮ የተቀረው ዓለም በህዋ ምርምር ሲራቀቅ እኛ የእለት እንጀራችንን ከበሬ ጫንቃ ላይ ባልተሻማን ነበር፡፡ አንድ ምእተ-ዓመት ያስቆጠረው ዘመናዊ ትምህርት ከተዘፈቅንበት የድህነት አረንቋ ሊያለቅቀን አልቻለም፡፡ ዛሬም ድረስ ድህነትን እንዳስታመምን፣”የረሀብን ጉንፋን እንደሳልን”፣በየሰዉ በረሀ በስደት እንደተንጠራወትን እናም ሌላም ሌላም እንደሆን እንዳለን አለን፡፡ ግን ለምን? በአንድ ሀገር ነባር ወግና ባህል እንዲሁም የአስተሳሰብ ደረጃ ላይ ተንተርሶ አለምአቀፋዊውን እውነታ ባገናዘበ መልኩ የተቀረጸ የትምህርት ስርአት ተፈላጊውን የባህሪ ለውጥ ማምጣቱ እሙን ነው፡፡ ከዚህ አንጻር እኛ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ያመራንበት አግባብ ተገቢው መደላድል የጎደለው ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡ ቤተክህነት መር የነበረው ባህላዊው የትምህርት አሰጣጥ ሂደት በምእተአመታት ቆይታው የጎለበቱ ሀገራዊ እሴቶችን ማካበቱ የሚካድ አይደለም፡፡ ነገር ግን ወደ ዘመናዊው ትምህርት የተደረገው ሽግግር የህብረተሰቡ የአስተሳሰብ ደረጃ መገለጫዎች የሆኑ የባህላዊው ትምህርት ትሩፋቶችን በወጉ ባገናዘበ አኳኋን አልነበረም፡፡ ለምሳሌ በአብነት ትምህርት ቤቶች ያለፈ ልበ-ብሩህ ወጣት ያለበትን አውድ እና ዘመኑን የዋጀ ቅኔን ያለብዙ መቃተት ሲዘርፍ ይታያል፡፡ መቀኘት በባህሪው ላቅ ያለ የፈጠራ አቅምን መጠየቁ አከራካሪ አይደለም፡ ፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ የአብነት ትምህርት ቤቶች የሚከተሏቸው የመማር ማስተማር ሂደቶች የፈጠራ ክህሎትን የሚያስጨብጡ ናቸው ለማለት ይቻላል፡፡ መቼም ምንም ቢሆን ይዘገይ ይሆናል እንጂ ለሀገር ቀን አይመሽም፡፡ እናም የትምህርት ስርዓታችንን ከማንነታችን ጋር በተዋሀደ መልኩ ለእድገታችን እንዲበጅ አድርገን ብንከልሰው መልካም ነው፡፡ ገጾች በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር በየ 15 ቀኑ የሚታተም መጽሔት ነው ፡፡ ተምሳሌት መጽሔት በኢትዮጽያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ምዝገባ ቁጥር 279/2006 እና በንግድ ምዝገባ ቁጥር kik/ AA/2/0003278/2007 ሐምሌ 15 ቀን 2006 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡ ዋና አዘጋጅ ንጉስ ይልማ አድራሻ: ክ/ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር [email protected] ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከድር አህመድ [email protected] ኤዲቶሪያል ቡድን ደሳለኝ መኩሪያ [email protected] አዲስ ፀጋዬ [email protected] በለጠ ጌታቸው [email protected] አለማየሁ ስሜነህ [email protected] አምደኞች ጽጌሬዳ መላኩ አላምረው (የእናት ልጅ) ክቡር መተኪያ ሄኖክ ሰይፉ ዲዛይን የኮምፒዩተር ጽሁፍ አዜብ ዓለማየሁ [email protected] አክራሞት መምህርነት የተከበረ ሙያ ነው! 3 የኛ ተምሳሌት “ከኢትዮጵያ ስወጣ እድሜ እቀንሳለሁ” ቴክኖ-እመርታ በእጅ የያዙት ወርቅ የኔ ሃሳብ ንቃ ያለው! አሳታሚ ኤኬቢዲ የፕሬስ የማስታወቂያና የማማከርአገልግሎት ገጽ ለገጽ በኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ 11 12 እስቲ ላ’ንድ ቀን 4 ጋን በጠጠር ይደገፋል! ፈታ በሉ ‹‹ሰሌዳው ተበይዷል›› 6 7 ገበያ ስርጭት እና ክትትል ዮርዳኖስ በቀለ የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 3277 ዘርሽታ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 212 ስልክ ቁጥር 251 911225298 ፖ.ሳ.ቁ 54154 ኢ-ሜይል [email protected] ስለ ሕግ ሲነሳ የተምሳሌት ማስታወሻ ፊቸር ትምህርት ምን ያህል ይፈጃል? 9 የቃሊቲ የሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ትዝብት የተሜ ገጽ 13 15 16 21 22 የቁጥር ጫወታ፤ ቁምነገር፤ ተዓምር እና ሳቅ 2