TEMSALET m jun, 2015 | Page 14

‹‹ሰሌዳው ተበይዷል›› በጽጌሬዳ ታ ክሲ ውስጥ ነኝ፡፡ ከሹፌሩ ኋላ፡፡ ማለዳ 1ሰአት አካባቢ፡ ፡ ሁሉ ወደየጉዳዩ ለመሄድ ከቤቱ የሚወጣበት ሰአት በመሆኑ ከመነሻው በመግባቴ ጥሩ ቦታ አገኘሁ እንጂ በየጎማውና በየሞተሩ ላይ ተቀምጦመሄድ ልማዴ ነበር፡፡ መቼ እንደጀመረኝ እንጃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለድምፆች ትኩረት እሰጣለሁ፡፡በሙዚቃ መሃል በሰዎች ንግግር መሃል ለብዙዎች ያልተሰሙ ቢሰሙም ችላ ተብለው የሚታለፉ ድምፆች ጎልተው ይሰሙኛል፡፡ እዚህም የመኪናው ሞተር ይጮሃል፡፡አልፎ አልፎ ከታክሲዋ ሆድ በሚወጣው ጡሩምባ ታጅቦ ችፍፍፍ የሚል የሃምሌ ዝናም ከጣሪያው ይሰማል፡፡(በበጋው ወቅት ወደ ሰማይ የተነነውን አቧራ ያየ ተጠራቅሞ ዘንድሮ በክረምት ከአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ጭቃ እነደሚዘንብ ቢተነብይም ትንቢቱ አልሰራ ኖሮ ይኸው ቀደሞ የምናውቀው ዝናም ራሱ ከሰማይ ይወርዳል)፡፡ ጋቢና ከሹፌሩ አጠገብ የተቀመጠው ሰው ትከሻውን እያርገፈገፈ ያለማቋረጥ ይስላል-ብርዱ ነው መሰል፡፡እዛው ጋቢና ከሱ በስተቀኝ ያለው ብላቴና ኪሱን እየዳበሰ ”ከዚህ ሜክሲኮ ስንት ነው?” ብሎ ጠየቀ አንገቱን ወደ ሹፌሩ አስግጎ፡፡ “እሱን ጠይቀው” አለ ሹፌሩ በአውራ ጣቱ ወደ ረዳቱ እየጠቆመ፡ ፡ሆ! አሁን እውነት ሳያውቀው ቀርቶ ነው?ሆን ብሎ ነው እንጂ ሲሸፍጥ፡፡አንዳንድ የታክሲ ሹፌሮች ታሪፍ ሲጠየቁ ደረጃቸውን ወደ ረዳትነት ዝቅ ያደረጉባቸው ይመስል እንደሁ እንጃ ቅር ይላቸዋል፡፡ ለመመለስም ያቅማማሉ፡፡ልክ አንዳንድ ሴት ዶክተሮች ነጯን ጋወን በመልበሳቸው ምክንያት “ሲስተር”“ነርስ” ሲባሉ ቅር እንደሚላቸው አይነት ይመስለኛል ስሜቱ…የረዳትን ለረዳት የምን ማምታታት ነው? እንዲያውም ለስራ ፈጣሪዎች የሚሆን አንድ ሃሳብ አለኝ፡፡ የታክሲ ረዳቶች ማሰልጠኛ ቢኖርስ? አዎ ስለ ደንበኛ እና ገንዘብ አያያዝ፤ ስለ አጠራር አይነቶች፤ የሰፈር ስሞችን በቀላሉ የማወቅ ዘዴ፤ስለ መልስ አሰጣጣጥ እና ሂሳብ ስሌት፤የረዳቶች የልምድ ልውውጥ…እንደ ሞያ የተወሰነ ስልጠና ቢኖረ b