TEMSALET m jun, 2015 | Page 12
ይህ ዓምድ የተለያዩ በማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ
የራሳቸውን አስተያየት በሚሰጡ አካላት ስፖንሰር
የተደረገ ነው
ስለ ሕግ ሲነሳ
እስቲ ላ’ንድ ቀን
ጋን በጠጠር ይደገፋል!
በዝግጅት ክፍሉ
እ
ንደው አንዳንዴ.. ምን አንዳንዴ በ’ለት ተዕለት
ኑሮአችን የሚደረጉ ድርጊቶች ፍትሐዊ አልሆን ብሎን
ተበሳጭተን.. እርር ድብን ብለን.. አልቅሰን
ባ’ቅመ-ቢስ ስሜት ውስጥ ሆነን ወደ ሰማይ አንጋጠን
አናውቅም ? ወደ ላይ ካንጋጠጥንበት ቦታ አንጀት የሚያርስ ነገር
ወዲያው ባለማግኘታችን እንዲሁ ንዴታችን ሰማይ ጥግ ደርሶ
አያውቅም ? ታዲያ ይህቺ ምድር ፍትሐዊ አይደለችም ብላችሁ
ደምድማችኋል ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ አንዳንድ ሰወች የሚያደርጉት
ሰምሮላቸው .. የተናገሩት ተደምጦላቸው የገደሉት ያስገደሉት
#ተቀብሮላቸው; ወደ ሰማይ ቢያንጋጥጡም ያው እንደ ምድራዊ
ህይወት ሁሉ ተሳክቶላቸው ሁሉ በ’ጃቸው ሁሉ በደጃቸው ሆኖ ሲታይ
በ’ነርሱ ዘንድ ምድር ፍትሐዊ ፍርድም አምላካዊ መሆኑ አምነው
ደምድመዋል ፡፡
ግን፤ ግን ሕግ፤ ፍትህ ምንድን ነው ? .. ሁሉም ሰው ሊያስማማ
የሚችል ትርጓሜ ወይም ፍቺ አልተገኘም ፡፡ በየዘመኑ የተነሱ የሕግ
ፍልስፍና ት/ቤቶች / School of thoughts / የራሳቸው
ትረጓሜ እየሰጡ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ወጥነት ያለው ሁሉንም
ሊያግባባ የሚችል ትርጉም አልተገኘም ፡፡
ሕግ መካኒካል ባህሪይ አለው ብለው የሚያምኑ ሰወች ለዚህ
እምነታቸው የሚያቀርቡት ማስረጃ ባ’ዋጅ ወይም በሕግ ድንጋጌ
መግቢያ ላይ እንዲህ ማለት ሌላ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረሰ
እንዲህ ማለት ነው ተብሎ የተሰጠውን ትረጓሜ ከሕግ መሰረታዊ ፍቺ
ጋር አጣምረው ሲተረጉሙት ይስተዋላል ፡፡ በሕግ ቋንቋ አንድ ሲደመር
አንድ አንድም ሁለት ፤ አንድም አስራ አንድ የሚሆንበት አጋጣሚ
ብዙ ነው ፡፡ ይህ አረዳድ ከህግ ጋር ተዛምዶ ለሌላቸው የማህበረሰቡ
ክፍሎች ከአመክንዮ (ሎጂክ) ውጪ ነው ፡፡ ይሁንና በዚህ ርዕስ በሌላ
ጽሁፍ የምንገናኝ መሆኑን በማስታወስ ወደ ዛሬው ጽሁፌ ተሸጋገርኩ ፡፡
የፍጥረታት ሁሉ መኖሪያ የሆነችው ምድር ምንም እንኳ ፍትሐዊ
አይደለችም ብለን ብናማርራት እና ብንወቅሳት እስቲ አንድ ጥያቄ
አንስተን መልሳችን ለራሳችን ትዝብት እንተዉ ፡፡ የሰው ልጅ በሕግና
በስርዓት ለመመራት ባይመርጥ ኖሮ ሕይወቱ ምን ሊመስል
እንደሚችል አስበነው እናውቅ ይሆን ? የሰው ልጅ በሕግና በስርዓት
ባይተዳደር ኖሮ ዕጣ ፈንታው ምን ሊሆን እንደሚችል አስቦት ያውቅ
ይሆን ? እስቲ ለአንድ ቀን መንግስት ሀገሩን የሚያስተዳድርበትን
ሕግጋትና
መመሪያዎች ሁሉ ለአንድ ቀን ብቻ ተግባራዊ እንዳይሆኑ አፈጻጸማቻን
ሁሉ አግጃለሁ የሚል አዋጅ ቢደነግግ ምን አይነት ሁኔታ ሊፈጠር
እንደሚችል በዓይነ-ህሊናችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ ? እስኪ
ሕግና ስርዓት የሌለበትን የዚህን ቀን ውሎ በዓይነ-ህሊናችን ለመቃኘት
እንሞክር ፡፡
11
በዚህ ቀን ሰው ሁሉ በሽብር፤ በፍርሃት፤ ባለመተማመን፤ በዕልቂት፤
በአጠቃላይ በስርዓት አልበኝነት ቀኑን ሁሉ አይነተኛ ባህሪው አድርጎት
ይውላል ፡፡ ከመኖሪያ ቤቱ እንጀምር .. በአንድ ቤተሰብ ከሚኖሩ
አባወራ ወይም እማወራ አንደኛው በሰላሙ ጊዜ ያስቀየመውን ቂም
በመበቀል ይጀምራል ፡፡ አንተ’ኮ…. አንቺ’ኮ በዛን ወቅት ያደረከኝ፤
ያደረግሽኝ…