TEMSALET m jun, 2015 | Page 10
ገጽ ለገጽ
ገጽ ለገጽ
በኤስ ኦ ኤስ የህጻናት
መንደሮች በኢትዮጵያ
የቃሊቲ የሙያ
ማሰልጠኛ ኮሌጅ
በዝግጅት ክፍሉ
በዚህ አጭር ቃለ-ምልልስ ኤሰ ኦ ኤስ በአትዮጽያ ያሳለፈውን 40 ዓመት መዳሰስ እጅግ በጣም ከባድ ነው ፡፡ ይሁንና ከአቶ ወርቅነህ
ንጉሴ የኤስ ኦ ኤስ የቴክኒክና ሙያ ት/ቤት ዲን ከተምሳሌት ጋር ያደረጉትን አጭር ቆይታ ለአንባቢ በሚመች መልኩ ቀንጨብ
አድረገን አቅርበነዋል ፡፡ ወደፊት የኮሌጁን አጠቃላይ የትምህርት አሰጣጥ እንዲሁም ተደራሽነት በስፋት የምንመለስበት መሆኑን
በዚህ አጋጣሚ ለአንባቢዎቻችን ለመግለጽ እንወዳለን ፡፡
ስለ ኤስ ኦ ኤስ አለም ዓቀፍ የሕጻናት መንደሮች አጠር ያለ
ማብራሪያ ቢሰጡን?
የኤሰ ኦ ኤስ ዓለም አቀፍ የሕጻናት መንደሮች ዓለም አቀፍ
ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን የዛሬ 60 ዓመት በ1949 ዓ.ም
(እ.አ.አ) በፕሮፌሰር ኸርማን ሜየር በተባሉ ግለሰብ በኦስትሪያ
ተመሰረተ ፡፡ ወቅቱም 2ኛ የዓለም ጦርነት ማብቂያ እንደመሆኑ
በጊዜው በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ህይወት በመጥፋቱ ምክንያት የብዙ
ቤተሰቦች እና ዘመዳሞች አድራሻ በመጥፋቱ ግለሰቡ በዚህ አስከፊ
ወቅት የተጎዱትን በመደገፍ እና የተጠፋፉትን በማገናኘት የራሳቸውን
አስተዋጽዎ ለማድረግ ታስቦ የተቋቋመ ተቋም ነበር ፡፡ ይህንን መሰረት
አድርጎ የተቋቋመው ኤስ ኦ ኤስ የስራ አድማሱን በማስፋት በአሁኑ
ወቅት ሃገራችንን ጨምሮ በ134 አገሮች ላይ እየሰራ ይገኛል ፡፡
በቅርቡ ፋይናንሻል ታይምስ /Financial Times/ በተባለ
ታዋቂ የፕሬስ ድርጅት ባደረገው ጥናት ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት
በዓለም ላይ ከሚንቀሳቀሱ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በአቅም እና በበጎ
አድራጎት 33ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ኤስ ኦ ኤስ በሃገራችን መቼና በምን ሁኔታ ሥራ ጀመረ?
ኤስ ኦ ኤስ በኢትዮጽያ የዛሬ 40 ዓመት በ1974 ዓ.ም
(እ.አ.አ) በሃገራችን ተከስቶ በነበረው ድርቅ በተለይም በትግራ