Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 40

ላይ የተመረኮዘው Baby and Child Care የሚለው መጽሐፍ በ1946 ተወዳጅና ታዋቂ በሆኑት የህጻናት ሐኪም በዶ / ር ቬንጃሚን ስፓክ ( Dr . Benjamin Spock ) ተዘጋጅቶ ቀረበ ::
የዚህም መጽሐፍ ዋና ሐሳብ ፥ ስለልጆች ጤና ቢሆንም በመጨረሻዎቹ ምእራፎች ላይ የሰፈሩት የልጆች አያያዝ ዘዴዎች ፥ በዛን ጊዜ በሚኖሩት ማለትም በልጅነታቸው በወላጆቻቸው ተቀጥተው ባደጉት ወላጆች ዘንድ በጣም ተቀባይነትን አገኘ :: የዚህ አዲስ ሐሳብ ቃል እንደሚከተለው ነበረ ::
“... ህፃኑን እንደ አዋቂ ሰው አክብራችሁና እንደ ጓደኛ አይታችሁ በፈለገው አይነት የራሱን መንገድ እንዲከተልና ነፃ እንዲሆን ልቀቁት :: አካባቢውን ከሚጎዳ ነገር ነፃ አድርጋችሁለት Explore ያድርግ :: በራሱ መንገድ የፈጠራ ችሎታውን ያዳብራል ..”::
የሚገርመው ነገር ግን ፥ እኚሁ ዶ / ር ከ 11 ዓመታት በኋላ ይሄንኑ መጽሐፋቸውን revise አድርገው በ1957 ሲያወጡት ይሄንን የልጆች አያያዝ ዘዴ ምክራቸውንም አሻሽለው “... ልጆች በወላጅ የሚሰጥ ጥብቅ ስነስርአት ያስፈልጋቸዋል ...” ብለዋል ።
ዳሩ ግን ላለፉት 11 ዓመታት በDr . Benjamin Spock ተሳስተው ብዙዎች ልጆቻቸውን በስርዓት አልተንከባከቡም :: ልጅ ወይም ሰው ደግሞ እንደ ላቦራቶሪ አይጥ ወይንም ኬሚካል ተሞክሮበት አይጣልምና ትውልድ ተበላሸ ::
ቀጥሎም በዚህ በተቀጣጠለ እሳት ላይ ቤንዚን የሚያርከፈክፉ ሌሎች ሁለት ሁኔታዎች ተከስተው ነገሩን
40
ሲያባብሱት እናያለን ::
እነዚህም ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው ::
1 . ጁን 25 , 1962 የአሜሪካን ኤትየስትስ ሕብረት መስራችና ፕሬዚዳንት የሆኑ Madalyn Murray O ’ Hair የተባሉ ሴት እኔ አማኝ ስላልሆንኩ ልጄ እንዲጸልይ አልፈልግም በማለት ሜሪላንድ የሚገኘውን የህዝብ ት / ቤት ( public school ) ከሰው ስላሸነፉ ይህንኑ ሃሳብ ሌሎች አላማኞች የሆኑ ሰዎችን አስተባብረው ከሜሪላንድ ስቴት ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው ከአሜሪካ ት / ቤቶች በሙሉ ጸሎትን አሳገዱ :: ሳልጠቅስ ማለፍ የማልፈልገው ነገር ይህ በሱ ምክንያት ፀሎት የታገደበት ልጅ ዛሬ የጌታ አገልጋይ እና “ እንፀልይ ” የሚል መጽሐፍ ደራሲ ነው ::
2 . ከዚህ በመቀጠል ደግሞ የሴቶች መብት እንቅስቃሴ በመጀመሩ ፣ እናቶች በቤት ውስጥ ሆነው ልጆቻቸውን መንከባከብና በፍቅርና በስርዓት ማሳደግ ቀርቶ ከቤት ወጥተው መስራት የተለመደ እየሆነ መጣ ::

በክርስቲያን ግለሰቦች የተደረገ ጥረት

1 . Dr . James Dobson
ይሄን አዲስ አስተሳሰብና ተከትለው የመጡት ሁኔታዎች በወጣቶች መካከል ያስከተሉትን የሞራል ውድቀቶች በመቃወምና ሁኔታውን በማጋለጥ ቀዳሚነት ስፍራ የያዙት ዶ / ር ጀምስ ዳብሰን ናቸው :: እኚህ ወንድም በ1970 ዓ / ም የመጀመሪያውን “ ለመቅጣት
ድፈር ” የተባለውን መጽሐፋቸውን አሳተሙ :: በዚህ መጽሐፋቸው ውስጥ ያሰፈሩትን ዋና ቁም ነገር ስናየው : -
“... ልጆቻችንን እየቀጣን ማሳደግ ሥርዓት ከማስያዙም በላይ ፥ የአባቶቻችንን አምላክ እግዚአብሔርን ለምንወዳቸው ልጆቻችንም ማስተዋወቅ ነው ::...” ብለዋል :: ቀጥለውም “... በ1960-70ዎቹ መሐከል ባለው ትውልድ ውስጥ የተነሳው የሂፒ እንቅስቃሴ እና የወጣቶች በወላጆች ላይ ማመጽ የመጣው በዚህ ልጆችን ገደብ የሌለው ነፃነት ስጡ በሚለው መመሪያ ያደጉት ልጆች ለዩኒቨርስቲ በደረሱበት ጊዜ ሲሆን ፥ ሃያሲያን ( Critics ) ምክንያቱ የዶ / ር ስፖክ መጽሐፍ ነው በማለት ይኮንኑታል ።”
ዶ / ር ዳብሰን ትግላቸውን በመቀ ጠል በ1977 ዓ . ም በቤተሰብ ላይ እናተኩር ( Focus on The Family ) የተባለውን ድርጅት በማቋቋም በእግዚአብሔር ዓላማ የተመሰረተን ቤተሰብ መንከባከብና መጠበቅ ብሎም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በዓለም ማሰራጨትን ዋነኛ አላማቸው አድርገው መንቀሳቀስ ጀመሩ ::
2 ) Dr . David Barton
እኚህ ወንድም በ1962 ማለትም ፀሎት ከሕዝብ ት / ቤቶች ከታገደ ከ15 ዓመታት በኋላ የወጣቶች አካሄድ በጣም አነጋጋሪ ሁኔታ ላይ መድረሱ ያሳሰባቸው ግለሰብ ከመንግስት መ / ቤቶች የተገኘ መረጃ ( information ) በማሰባሰብ የወጣቱን የሞራል ውድቀት በስታትስቲክስ አስደግፈው “ America pray or not to pray ” የሚል መጽሐፍ አውጥተዋል :: በመጽሐፋቸው ላይ ካሰፈሩት Statistics ለምሳሌነት ብንጠቅስ : -