Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 24

በማድረግ ስህተት እንሰራለን ። ሆኖም ግን ሊሰሙት ለሚወዱና ለመስተካከል ፈቃደኛ ልብ ላላቸው ፤ አስተካክሎ ፍሬያማ ለማድረግ ጌታ ሁሌም ዝግጁ ነው ። ዛሬ ላይ ቆመን ትላንት ትዝ ሲለን በጸጸት እንሞላለን ። ያለፈውን ስህተታችንንና ያስከተለውን ውድቀት ስናስብና አሁን እየተለማመድን ያለውን የእግዚአብሔርን ፀጋ ስናይ በውድቀት ያሳለፍነው ጊዜ ይቆጨናል ።
በርግጥ እግዚአብሔር የት ላንት ሕይወታችንም አምላክ ነው ። ያለፈውን ትዝታ የሚያመጣው ለወደፊት መንፈሳዊ ሕይወታችን እድገት እንዲሆን ነው ። እርሱ ባይረዳንና እጃችንን ይዞ ባያወጣን የወደቅንበትን ጭቃ እያቦካን በዛው የስህተት አረንቋ ውስጥ እንከርም ነበር ። ሆኖም ጌታ ክንደ ብርቱ ስለሆነ ሲያሻግረን ያለፈውን የልጅነት ዘመን ውድቀትና ድክመት ፈጽሞ በማስወገድ በህሊናችን ላይ አሻራውን እንዳይተው አድርጎ ነው ። እውነት ነው ለብዙዎቻችን የሚያስቆጩ ወርቃማ የምስክርነት እድሎች አምልጠውናል ። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ያለፈውን አለማወቅ ፣ ድክመትና ጸጸት ለውጦ የወደፊት ሕይወታችን የሚመሰረትበት አስተማማኝ መሰረት ሊያደርገው ይችላል ።
መመለስ የማንችለውን ያለ ፈውን ዘመን ትተን ፣ በእግዚአብሔር ምህረት በዕድሜያችን ላይ በ ተጨመረልን ዘመን በማስተዋል ከጌታ ጋር አብረን ለመስራት እንነሳ ። ለክርስትያኖች በምድር ሳለን ብቻ ልናደርገው የታዘዝነው ነገር ላልዳኑት መመስከር ነው ። በሰማያዊው ዓለም እንመስክር ብንል
24
እንኳን የምንመሰክርለት ያልዳነ ሰው አናገኝም ። መስክረው ሰዎችን ወደ ጌታ ያመጡት በሽልማታቸው ሲደምቁ አይተን መመስከር ቢከጅለን እንኳን የሚታሰብ አይደለም ። ታድያ ብዙዎች ይህን ዕድል በምድር ሳሉ ለምን አይጠቀሙበትም ብለን ስንጠይቅ ፣ ተግዳሮቶቹን ማየት ግድ ይለናል ። Everyday Evangelism የተባለው አገልግሎት በ2016 በሰሜን አሜሪካ ያደረገው ጥናታዊ መረጃ “ 95 % የሚሆኑት ክርስትያኖች በዓመት ውስጥ ለአንድም ሰው አይመሰክሩም ” ይላል ። ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው “ በቂ አይደለሁም ” የሚለው ፍርሃት ሲሆን ሌላው ምክንያት ደግሞ “ ምስክርነትና ሰዎችን ወደ ጌታ መጋበዝ የተወሰኑ አገልጋዮች ስራ ነው ” የሚለው የተሳሳተ መረዳት እንደሆነ ይታመናል በማለት ጥናቱ ያስረዳል ።
በማያያዝም ከጥናቱ በመነሳት የአገልግሎቱ መሪ ሲናገሩ “ የዳኑ ክርስትያኖች እምነታቸውን ለሌሎች እንዴት ማካፈል እንደሚገባቸው ራሳቸውን ካዘጋጁ ወይም ስልጠና እና ትምህርት ከተሰጣቸው ፣ ምስክርነትን ያለማቋረጥ በደስታ ያደርጉታል ። በዚህ ተግባራቸውም አስደናቂ የሆነ ውጤትን ያያሉ ።” በማለት በአነስተኛ ዝግጅት እና ስልጠና ብዙ ፍሬዎችን ማየታቸውን ይገልጻሉ ። “ ክርስትያኖች እምነታቸውን እንዴት ለሌሎች ማካፈል ይገባቸዋል ?” በሚል ርዕስ ባካሄዱት ስልጠና በርካታ ክርስትያኖች በመንፈስ ቅዱስ በመታገዝ ከፍርሃታቸው ተላቀው የታላቁ ተልዕኮ አስፈጻሚ መሆን እንደቻሉ ይመሰክራሉ ።
ሌላው ለመመስከር ፈቃደኛ
የሆኑ ወገኖችን የሚገጥመው ችግር ሰዎች ለማዳመጥ ያላቸው ጊዜ በጣም አጭር መሆኑ ነው ። የምዕራባዊው ዓለም ነዋሪዎች ዘና ብለው ጊዜ በመስጠት ለማዳመጥ ፈቃደኞች አይደሉም ። ታድያ መስካሪዎች ለድነት መሰረታዊ የሆኑትን ትም ህርቶች ማለትም ፡ -
1 . ጸጋ ፦ የእግዚአብሔርን ነፃ ስጦታ ( ሮሜ 6:23 ፣ ኤፌ 2:8-9 )
2 . ሰው ፦ የሰውን ኃጢአተኛነት ( ሮሜ 3:23 ፣ ማቴ 5:48 )
3 . እግዚአብሔር ፦ ጻድቅ ፣ ህላዌና ልእልና ፣ ፍርድ እና ፍቅር ( 1 ዮ ፤ 4:8 )
4 . ኢየሱስ ክርስቶስ ፦ ፍጹም ሰው ፣ ፍጹም አምላክ ፣ ስለ ኃጢአተኛው መሞቱና መነሳቱን ፣ ( ዮ 1:1-14 , ኢሳ 53:6 )
5 . ተስፋ ፦
እንዲሁ
በማመን
የተሰጠንን
የዘላለም
ሕይወት
ተስፋ ( ያዕ 2:19 ፣ ሐዋ 16:31 )
በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እነዚህን አምስት መሰረታዊ ነጥቦች አስረድቶ ሰዎችን ጌታን ተቀበሉ ብሎ መጋበዝ ለብዙዎች አስቸጋሪ ነው ። ብዙዎቻችን የቃሉ እውቀት እንኳን ቢኖረንም በዚህ ዙርያ ራሳችንን በጸሎት ፣ ወይም በስልጠና ስላላዘጋጀን ጊዜ ወርቅ የሆነባቸው የምዕራቡ ዓለም ነዋሪዎች ሳይሰሙን አቋርጠውን መሄድ ግድ ይላቸዋል ። ያለ ዝግጅት ልንመሰክር ስንወጣ “ ቅኔ ሲጎድልበት ቀረርቶ ሞላበት ” እንደሚባለው መነገር የሚገባቸውን ቀጥተኛ አምስት እውነታዎችን ትተን ብዙ ጊዜ