AddisLidet 2017 | Page 17

የዳማ ጨዋታ
ሙግት በኤልቤቴል ተኮላ
ዳማ ሲጫወቱ ሰይጣንና ሰይጣን ፣ መሀል አስገብተው ጠጠራቸው አንተን ፣ ሲያሻቸው ወታደር ሲፈልጉም ንጉስ ፣ ወይም ተዋጊያቸው ባለ ብ ..... ዙ ፈረስ ፣ ባለወግ አድርገው ባለግርማ ሹመት ፣ በክብር አጅበው እያዩህ በስስት ፣ በጣታቸው ግፊት እየኮረኮሩህ ፣ ካንዱ ጫፍ አንዱ ጫፍ አለምን ሲያዞሩህ ፣ ስምህ በሀይል ገኖ የተደላደልከው ፣ “ Game Over ” እስኪሆን እስክትበላ ነው :: እኔስ አንተን ብሆን ከጠዋት ሲጀመር ፣ የሰይጣንን ሹመት አልፈልግም ነበር ::
ወይ ቅሌት !
በዶ / ር አዳም ቱሉ
ከዚህ ቀን ጀምሬ ባርካችሁዋለሁ ብለህ ያልከን የታል ዘንድሮም ትግል ነው የአምናውን ሩጫ ተያይዤዋለሁ እታገለዋለሁ ላፍታ ጋብ ሲል ፊትህ እቆማልሁ እጠይቅሃለው ፤ መች ነው ምባረከው ? ታምር የሚሆነው ? ለኔስ የወሰንካት በረከትህ የት ናት ? ምትገኘው በምድር ተከባና ኮርታ በስኬቶች ቅጥር እስቲ ላንጎራጉር ፧ እንደማስታገሻ ጥያቄ አለኝና በረከትን ስሻ በኔ ራሴ ጥበብ ፤ ሰፋ ባለው መንገድ ብሄድ ምን አለበት አንተ የምትመራኝ ፧ እንድሄድ በጠባብ እቅድህ ካሳቤ ይለያል በስፋት ወይ ጥበብህ የታል ? አቋራጭ አታውቅም ወይስ አትመርጥም ? በረጅሙ መንገድ ፤ ብሰላችም በጣም በአቋራጭ ቢቀድሙም ብዙዎቹ ሄደው ይሁን ይሰብስቡ ፤ የቻሉትን ሁሉ ያከማቹላቸው ፤ ለህዝበ ፃድቃኑ ለሚከተሉቱ ፤ የህይወትን መንገድ የምታገኛቸው ፥ በረከት ስትወርድ በቅንነት በጽድቅ በእውነት ልትፈርድ !
17